የምዕ/ጎ/ዞንና አካባቢው አማራ ልማት ማህበር ጽ/ቤት crisis-affected Children are protected from violence, exploitation, abuse, neglect, and harmful, practices ከተባለ ግበረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በወንበርማ እና ሰከላ ወረዳዎች እየሰራን እንገኛለን፡፡ለዚህ ተግባር ግብዓት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በሎት በመለየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ክፋያ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ምዕ/ጎ/ዞን አካ /አልማ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በምዕ/ጎ/ዞን/አካ/አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን፤ ጨረታው በዚሁ በ07 ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በ8ኛው ቀን ጧት 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ለሚሰራው ስራ የውል ማስከበሪያ 10በመቶ ሲፒኦ ካስያዘ በኋላ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎችን ወንበርማና ሰከላ ወረዳዎች ድረስ በመከፋፈል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የዕቃውን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊው እንደ አስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በሎት ድምር ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕ/ጎ/ዞንና አካባቢው የአማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት

