ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

0
117

የፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል 2017 ዓ/ም በጀት አመት የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ እና ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ግዥ ለመግዛት በዘርፉ ፈቃድ ያአላቸዉ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2017 በጀት ዓመት ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ እንዲሳተፋ ይጋበዛሉ፡፡

  1. የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ሰርተፍኬት ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሃያ አምስት ብር/ በመክፍል ግዥ ፋይናስ የሥራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቅናት በአየር ላይ የሚዉል ሲሆን በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ቢያሸነፋ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ የሚያሲዙ ይሆናል፡፡ የኤሌክትሮኒከስ ጥገና ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ የዉል ማስከበሪያ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በየገጽ በማድረግና በፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆሰፒታሉ ግዥ ፋይናስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀዉ የመጫረቻ ሰጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታዉ በአየር ላይ የሚዉለዉ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስ ቢሮ ከፍል ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አይሰተጓጉልም፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 16 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here