ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

0
58

በአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 ኮምፒተርና ተዛማጅ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6 ተገጣጣሚ የቢሮ እቃዎችን፣ ሎት 7 የህትመት ውጤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ገቢ ማድረግ ደረሰኙን ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  4. የእቃ ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ከደ/ማ/ከ/አስ/ፖ/መምሪያ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ከንቲባ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በማሸግ የተጫራቹን ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ በመፃፍ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ መልሶ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ዝግ ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ዉድድር የሚካሄደዉ በሎት (ጥቅል) ዋጋ ሲሆን ለሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት አለበት፣ ካልተሞላ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  10. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል በመያዝ አገልግሎቱን መስጠት አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ከእያንዳንዱ እቃ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. አሸናፊው በራሱ ትራንስፖርት የደ/ማ/ከ/አስ/ፖሊስ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. በጨረታ ማስታዎቂያውና በተጫታቾች መመሪያ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  14. በጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ የደ/ማ/ከ/አስ/ፖሊስ መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 49 48 11 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here