የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚያስፈልጉ የምግብ
እና መገልገያ እቃዎችን ሎት 1. ለምግብ አገልግሎት የሚዉሉ ሩዝ ፣ መኮረኒ ፣ የተዘጋጀ በርበሬ ፣ የተዘጋጀ ሽሮ ፣ቲማቲም ድልህ ወዘተ ፣ሎት 2. አትክልት፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ እንቁላል ወዘተ ፣ ሎት 3. የእርድ በሬ ፣ሎት 4. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 5. አላቂ እቃዎች ፣ሎት 6. የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 7. ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 8. ከነጭ ዱቄት የተሰራ ዳቦ ፣ ሎት 9. የኤሌክትሪክ እቃዎች የህንፃ መሳሪያና የቧንቧ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፡፡
 - የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
 - የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላችሁ፡፡
 - የጨረታ ግዡ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
 - ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 - የሚገዙ የእቃዎች፣ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
 - የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ወይም በባንክ በተመሰረተ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይቻላል፡፡
 - ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1 በመቶ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
 - ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባችሁ፡፡
 - ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
 - ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
 - አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
 - የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 - በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 46 84 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

