ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግጨ 01/2017

0
185

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የቋሚነት ባህሪ ያላቸውን እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ እቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችን፣ የፈርኒቸር እቃዎችን፣ የመኪና እቃዎችን፣ አገልግሎቶችን እና የብስክሌት ጎማ ከነ-ካላማዳሪው  ግዥ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች፡-

በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የእቃው/የአገግሎቱ ግዥ መጠን ብር ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር)  በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ  ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት  ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ አንደኛ ፎቅ ላይ  ቢሮ ቁጥር 01 ወይም 02 በአካል   በመቅረብ  የማይመለስ  200.00 (ሁለት መቶ ብር)  በመክፈል የጨረታ ሰነዱን  መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ  የድርጅቱን ህጋዊ  ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የመጫረቻ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኝው አብክመ ገንዘብ ቢሮ 6ኛ ፎቅ ትልቁ አዳራሽ  ላይ ይከፈታል፡፡

በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ለተወዳደሩበት እቃ /አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ውድድሩ የተጫራቾችን መመዘኛ መስፈርቶችን ከአሟሉት ተጫራች ድርጅቶች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት አሸናፊ ሁኖ ይመረጣል፡፡

የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here