ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 003/2017

0
174

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ በመደበኛና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት የውሃ ማጣሪያ እቃዎችን ተወዳዳሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

በዘርፉ  የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የእቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ  ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ እና  ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይቻላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ የሚወዳደሩበትን እቃ  ሁለት በመቶ  ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀ እና ኢነርጅ  ቢሮ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00  የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 በ8፡30  ላይ ይከፈታል፡፡

የጨረታ መዝጊያ ቀን 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 22 201 32 /058 220 10 78/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አብክመ ውሀ እና ኢነርጅ  ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here