ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 02/2017

0
105

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የሞዥን 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት G+1 የህንጻ ግንባታ ፣ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት 3 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት /ለመግዛት/ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. ማንኛዉም የሥራ ተቋራጭ የሞዥን 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት G+1 የህንጻ ግንባታ የመማሪያ ክላስ ግንባታዉን ለመስራት የሚሳተፉ ተቋራጮች GC/BC ደረጃ 7 እና በላይ ለሆነ ተጫራቾች መካከል አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
  2. የተሰጣቸው የንግድ ሥራ ፈቃድ 1 ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡ ቲን /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቫት/ ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ሁሉም የእቃ አቅርቦትና የግንባታ ሥራዎች ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የእቃ አቅርቦት ሥራዉን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መስራት /ማቅረብ/ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸዉን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገዉና ማህተም አድርገዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚፈለገዉ ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታዉ ላይ ዋናዉንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተዉ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ለዕቃ ግዥ በሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ለግንባታ ስራዎች በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
  6. እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ የገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡ ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ሽህ ብር/ ፣ለሎት 2 ብር 20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/፣ ለሎት 3  ብር 1,500.00 /አንድ ሽህ አምስት መቶ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታዉ ጋር ለብቻዉ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ስራ የጽሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ላሉት የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 06 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለዕቃ ግዥ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ለሞዥን 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት G+1 የህንጻ ግንባታ ሥራዎች ለ30 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ31ኛው ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን /ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. አቅርቦቱን ለማቅረብ /ለመስራት/ ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ በገቡት ውል መሰረት ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከአሸነፉበት ዋጋ ልዩነት ቢኖር ምንም አይነት ጭማሪ የማናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  11. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውንነ ፣ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  13. ተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊዉ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለዉል ማስከበሪያ የሚሆን ለዕቃ ግዥ አስር በመቶ እና ለሞዥን 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት G+1 የህንጻ ግንባታ ሥራዎች/ ሃያ አምስት በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለእቃ አቅርቦት ለአገልግሎት /ለግንባታ ሥራዎች/ 40 /አርባ ቀናት/ መሆኑን መገንዘብ አለበት፡፡
  16. ሥራዉን ለመስራት ዉል ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ ለእቃ አቅርቦት 15 ተከታታይ ቀናት እና የግንባታ ሥራዉን ለመስራት ዉል ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ 360 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 247 01 13 /058 247 05 09 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሸበል በረንታ ወረዳ ////ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here