ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
145

የምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ  ለዞኑ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1.የጽዳት መሳሪያ፣ ሎት 2.የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. የቀላል ተሸከርካሪዎች ጎማ፣ ሎት 5. የውጭ አገር ፈርኒቸር  ዕቃዎች ፣ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች  ሕጋዊ አቅራቢዎችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችልሉ::
  3. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ  1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ   ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሠረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት ከሎት 6. በስተቀር ሁሉም በእያንዳንዱ ዕቃዎች በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው:: የሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አሸናፊ የሚለየው በተናጠል ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ዝቅተኛ ያቀረበው ሲሆን  በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ዕቃዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል::
  7. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በ50.00 /ሃምሳ ብር/ የሚሸጥ ሲሆን ሰነዱን ከተቋማችን ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ::
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦድ ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው::
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ  በ4፡30  ታሽጉ በ5፡00  ይከፈታል:: እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ይከፈታል :: ተጫራቶች ቢገኙም ባይገኙም  ጨረታው ይከፈታል::
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝና ዕቃዎችን ምዕ/ጎጃም/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት::
  12. መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል:: መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ::
  14. ተጫራቶች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 08 95 በመደወል ማብራሪያ መቀበል ይችላሉ::
የምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here