ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተያዘው 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚገዛቸው የተለያዩ እቃዎች እና የሚያሰራቸው ስራዎች ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. ህትመት፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ ሎት 5. የህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 6. የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 8. ፈርኒቸር፣ ሎት 9. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 10. የጭነት አገልግሎት እና የሚያሰራቸው ስራዎች ሎት 11. የሆስፒታሉ የውስጥ የውሃ ፍሳሽ ሲስተም ብልሽት ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
3. ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፤ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
5. በግንባታ ሥራ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ እቃዎች እና የሚሰሩ ሥራዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃዎች ግዥ እና የጥገና ሥራ ብር ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በማሸግ ማስያዝ እና በጥቃቅን መ/ቤት የተደራጁ ከሆኑ ካደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ በአድራሻችን በመፃፍ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
10. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታ በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቡሬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ብሄራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
13. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሁለት በመቶ ይቀነሳል፡፡
14. ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅበቸዋል፡፡
15. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርገው ማስገባት አለባቸው፡፡
16. ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊው ተለይቶ ውል ከተያዘ በኋላ ከህትመት፣ ከግንባታ እና ከጥገና ውጪ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በራሱ ወጪ እስከ ቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
17. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 05 76 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
18. የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን በመምረጥ ነው፡፡

የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here