ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የደንብ ማስከበር የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግዥው መጠን ከ20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ቫት ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ ቆርጠን የምናስቀር ይሆናል፡፡
5. የሚገዙት እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤ ሁሉንም እቃዎች በኦርጅናል መሞላት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለአንድ ሎት ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 39 በመክፈል፤ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 46 ማግኘት ይቻላል፤ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበት ለሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ ፣ ሎት 2. የፕሪንተር ቀለም፣ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 3. የጽዳት እቃ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ሎት 4. የደንብ ልብስ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ ፤ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናል ሰነድ በግልጽ ፅሁፍ ኢንቨሎፕ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 46 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ::
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን በቢሮ ቁጥር 46 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
9. አሸናፊው የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ በሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ሲሆን የሎት አራት እና የሎት አምስት አሸናፊ የሚለየው በተናጠል ይሆናል::በዚህ መስፈርት መሠረት በሎት ለተጠቀሱት ሁሉም እቃዎች ዋጋ ያላቀረበ እና በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
10. ሥርዝ ድልዝ የበዛበት እና አጠራጣሪ ቁጥር ያለው የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስል/ቁ/ 058 220 93 73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here