ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሚዉሉ 1.የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች ፣ 2.የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ 3. የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸዉ መረጃዎችና የጨረታ ሰነዶች ግልጽና የሚነበቡ መሆን አለባቸዉ ፤ የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ የገ/ግ/ፋይ/ንብ/አስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. የጨረታ ሰነዱ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል/፤ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይፈፀማል፡፡
9. የንፅህና መጠበቂያና የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
10. የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች አሸናፊ የሚለየዉ በተናጠል ዋጋ ነዉ፡፡
11. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
12. ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት ሃያ በመቶ መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
13. አሸናፊዉ ድርጅት የሚያቀርበዉ እቃዎች ኦርጅናልነቱና ጥራት ሲረጋገጥ ንብረቱ ገቢ ይሆናል፡፡
14. አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎቹን ሐይቅ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በማስረከብ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 04 83 ወይም 09 14 60 89 56 እና 09 21 04 84 14 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሐይቅ ከተ/ መጠ/ ዉሃ/ ፍሳ/ አገ/ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here