የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የመኪና ጐማ ከነካላማዳሪው፣ የመኪና ዲኮር፣ የሞተር ብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው፣ የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው፣ ህትመት፣ የቢሮ መገልገያ፣ የጽዳት እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ነገር ግን ከላይ ከ 1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፤ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የመኪና ጐማ ከነካላማዳሪው ፣ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ የመኪና ዲኮር ፣ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የሞተር ብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ፣ 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/፣ የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ፣1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ህትመት፣ 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ የቢሮ መገልገያ፣ 4,000.00 /አራት ሺህ ብር/ የጽዳት እቃዎች ፣ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል የገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማለትም ህዳር 16 /2017 እስከ ህዳር 30 / 2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ተኛው ቀን ታህሳስ 1/ 2017 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
11. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ