ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

በአብክመ ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውልሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. የኤልክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 5. የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ሎት 6. የኤሌክትሪክና የግንባታ እቃዎች፣ በሎት 7. የመኪና መለዋወጫ፣ እቃዎች፣ ሎት 8. ለሰራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ የመኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ውል ይዞ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ትቫ) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 25 በመምጣት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድቦንድ/ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ-1በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም ፤የድርጅቱ ማህተም ፤አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል፤ ጨረታው ከወጣበት ከህዳር 16 /2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ጨረታው በ16ኛው ቀን ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
10. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
11. አሸናፊው ዕቃዎችን የሚያቅርበው ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል መጋዝን ይሆናል፡፡ ከታዘዘው ዕቃ ወይም ስፔስፊኬሽን ውጭ ቢያቀርብ በራሱ ወጭ ዕቃውን ወስዶ ቀይሮ ማምጣት አለበት፡፡
12. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
13. የባለሙያ ፍተሻ የሚያስፈልጋቸውን በባለሙያ ተረጋግጠው ወደ ንብረት ክፍል የሚገቡ ይሆናል፡፡
14. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፤ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
15. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
16. መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላይ ከተጠቀሱት ዕቃዎች ብዛት ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀናት ወይም ለሁለት ወራት ይሆናል፡፡
18. መ/ቤቱ አሽናፊውን የሚለየው በጥቅል ድምር /በሎት/ ዋጋ ይሆናል ፤በመሆኑም ተጫራቾች ሁሉም በጨረታው የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባችዋል፡፡
19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here