የመተማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን አድራሻ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ውሃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 ሥልክ ቁጥር 09 06 42 42 30 የሚመጣውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ወርሃዊ ኮታ 1562 ኩንታል ስኳር ውስጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንደሚመድብልን የኩንታል መጠን ከተለያዩ ስኳር ፋብሪካዎች ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ምዕ/ጎንደር ዞን ገንዳውሃ ከተማ ድረስ ማስመጣት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ሠነዱን ለመግኘት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍሎ ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ቀንና ሠዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከታወቀ ባንክ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በራሳቸው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው መጫረት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 12፡00 እና ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡30 ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የመጫረቻ ሠነድ ማስገቢያ ቦታ መተማ ሁለ/የገ/ህ/ሥ/ማ/የኒየን ቢሮ ቀርቦ የጨረታ ሳጥን በተዘጋጀበት ቦታ ማስባት ይችላሉ፡፡
የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀርቦ የሞላበትን የገንዘብ መጠን አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
ጨረታውን ያሸነፈ ትራንስፖርተር ለ6 ወር ለማጓጓዝ ውል የሚገባ መሆን አለበት፡፡
ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል /እሁድ/ ቢሆን በቀጣይ የሥራ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 09 10 85 53 74 /09 18 27 20 39 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን