በአብክመ የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በ2017 ዓ.ም አገልግሎት የሚዉሉ በግልጽ ጨረታ በሎት አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ይኸውም ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3 ጽዳት እና ሌሎች አላቂ እቃዎች እና ሎት 4 የመኪና እቃዎች መለዋወጫ ሲሆኑ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው ተጫራቾች ለመወዳደር የቫት ተመዝጋቢ መሆን ለሚያስፈልጋቸዉ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወ/ሙ/ብ/ም/ማ/ክ/ማ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የፕሪንተር ቀለሞች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ኦርጅናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር ማስሞከር፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ መጥተው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ከነ ቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ቫትን ያላካተተ ዋጋ ቫት እንደተጨመረ ተደርጐ ስለሚወሰድ አልጨመርኩም ወይም ይጨመረበት የሚል ተጫራች ቢኖር ተተባይነት አይኖረውም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ ፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመ/ቤታችን የግ/ፋ/ን/አ/ በድን በመምጣት የማይመለስ /ሀያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከ23/03/2017 እስከ 07/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው ከሎት 1-4 በ07/04/2017 ዓ.ም 11፡30 ታሽጎ 08/04/2017 ከጠዋቱ በ3፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በጨረታው ያልተገኙ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን የመቀበል ግዴታ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለክላስተር ማዕከል ማሳወቅ አለባቸዉ፡፡
ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በመ/ቤታችን ፋይናንስ ገቢ በማድረግ የደረሰኝን ፎቶ ኮፒ በፖስታዉ ዉስጥ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ኦርጅናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረክቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፣ በህግም ያስጠይቃል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 431 51 15 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል