ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት የሚውል፡- የጽህፈት መሳሪያ እና የስፖርት እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ክፍያ መለያ /ቲን/ ቁጥር ያላቸው፡፡
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ /ሰፔስፊሌሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በሚወዳደሩበት የዕቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ደብር ታቦር ከተማ አስ/ገን/ መምሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዥ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ስም ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለፅ በደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርበዎታል፡፡
ጨረታው በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት እለት በዓል ቀን ከሆነ የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ስዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለፅ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ /ተመስርቶ/ መጫረት አይችልም፡፡
የጨረታ መዝገጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንደም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
የእቃው መጠን እስከ ሃያ በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደ/ታ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ/ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 02 09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here