ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
105

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የደ/ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2017 በጀት አመት ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የተለያዬ ህትመቶች እና ሎት 4 ቋሚ አላቂ እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት እና በህትመት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ የሚወዳደሩ ተጫራቾች፡-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ይህ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ በመምጣት ከዋናዉ ጋር ሊገናዘብ የሚችልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ 25.00 /ሃያ አምስት ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት /ቢድ ቦንድ/ ብር በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በባንክ ያሳዙትን ገንዘብ /ሲፒኦ/ ወይም የጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገዉ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ብለዉ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ እስከ 16ኛዉ ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የሚታሸገዉም በዚሁ ሰዓት ነዉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባገኙም በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ 16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡45 ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ይከፈታል፡፡
የጨረታ አሸናፊዉ የሚሆነዉ በጥቅል /በሎት/ ነዉ፡፡ ነገር ግን ከቀረቡት እቃዎች አንድም እቃ ያልሞላ ከዉድድር ውጭ ነዉ፡፡
የሚገዙ እቃዎች ርክክቡ የሚፈፀመዉ በሙያተኛ ተረጋግጦ ነዉ፡፡
አቅርቦት ደጎ/ዞን/ደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ይሆናል፡፡
የሚገዙት እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ በስልክ ቁጥር 058 141 71 78 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ተቋሙ ግዥውን ከቀረበዉ የዋጋ መጠን ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አሸናፊዉ የአሸነፋቸዉን እቃዎች በራሱ ወጭ በመጓጓዝ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ማቅረብ አይችሎም፡፡

የደ/ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here