የጨረታ ቁጥር አብክመ/የወ/ኩ/ም/አገ/ብግጨ/03/2017
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት እና ፑል ተጠቃሚ ለሆኑት የመንግስት ልማት ድርጅቶች መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ መ/ቤቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 406 ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 406 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 403 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 058 320 31 68 ፋክስ 058 320 11 83 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት