ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
148

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሃል አስፓልት አካፋይ የብረት አጥር ግንባታ በግልጽ ጨረታ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ሥራዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመልስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመሥሪያ ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና  ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ  ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ገንዘብ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን ማቴሪያሎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል  ዋጋ  ይለያል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ/ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5  ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን ሥራዎች ሃያ በመቶ ከውል በፊት የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ሥራዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  17. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
  18. አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  19. ከአሸናፊው ድርጅት ሃያ በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  20. ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማፅደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስገሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ60 ቀን ይሆናል፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት /ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here