ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
100

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም ሎት 1 የጽፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 ፈርኒቸር፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5 ጽዳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዛው እቃ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ከ23/3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ፖስታው በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በታሸገ ፖስታ ባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ08/4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾቹ ከአሸነፉበት ቀን ጀምረው ውል በመውሰድ ሥራ መጀመር ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች እኛ በሠጠናቸው ዋጋ አሸንፈው በሚመለከተው መሠረት የእያንዳንዱን እቃ /አገልግሎት/ ብዛት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ እስከ ሃያ በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ዝቅተኛ ጠቅላላ ዋጋ ድምር ያቀረበዉን ነው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 21 ወይም ስልክ ቁጥር 058 226 65 11 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here