ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ4ቱም ፑል መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፤ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ቋሚ አላቂ፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 ህንፃ መሳሪያ እና ሎት 6 ኮድ LN-166 የመኪና እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለዉ መነበብ መቻል አለባቸው፤
የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ23/03/2017 ዓ.ም እስከ 08/4/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታዉ በ08/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል) የጨረታ መክፈቻ ጊዜዉ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች ሰነድ ላይ ከአንድም ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
አሸናፊው የሚለየዉ በሎት /በድምር/ ዋጋ ነዉ፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናሉ፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት እቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
ጨረታዉን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታው እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here