የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/02/2017
በአብክመ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ቢሮን መልሶ ለማደራጀት፣ ፈርኒሽ ለማድረግና ለማስዋብ የዲዛይን፣ የሥራ ዝርዝርና የመጫረቻ ሰነድ ለማሰራት በመስኩ የተሰማሩ ደረጃ 2 እና በላይ የሆኑ /BUILDING COUSUITant /Atchitees Consulting ድርጅቶችን በውስን ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው::
የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ::
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
መልሰው የሚደራጁ የሥራ ክፍሎችን በአካል በማየትና ልኬታ በመውሰድ መልሶ ለማደራጀት፣ፈርኒሽ ለማድረግ ለማስዋብ የሚፈለግ ዲዛይን፣ የስራ ዝርዝር፣ፈርኒሽ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ዝርዝር በየክፍሎች በመዘርዘርና ጠቅላላ የጨረታ ሰነድ ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን የሙያ ዋጋ በመሙላት መወዳደር ይቻላል::
አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዲዛይን፣ የስራ ዝርዝርና የጨረታ ዶክመንት በተሟላ መልኩ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ ይሆናል::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይ /ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናትማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አገልግሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ ቴክኒካሉን እና ፋይናንሻል በተለያ ፓስታ በማሸግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው ከወጣበት ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት በ21ኛ ቀን እስከ 8:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ21ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን