በአብክመ የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ለሁለተኛ ጊዜ በሎት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ የቫት ተመዝጋቢዎችን ብቻ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
ተጫራቾች አገልግሎቶችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ፈቃዱ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግዥው አመታዊ የምግብ አቅርቦትተ መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸ በኋላ ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸው ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በ5፡00 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058 661 02 64 ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 03 30 ይደውሉ፤ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች አሸናፊው ከተለየ በኃላ የሚመለስ 4‚000.00 /አራት ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል