የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 ፈርኒቸር፣ ሎት 3 መጋረጃ እና ሎት 4 የጽህፈት መሳሪያ (ለስልጠና አገልግሎት ሚውል) እቃዎች በአንድ ጊዜ ውል ተይዞ የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ አንድ መቶ ብር በየሎቱ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ /በኦንላይን/ ከወጣበት ከህዳር 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 23/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 08/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ታህሳስ 08/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በስራ አመራር ኢንስቲትዩት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት