ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

የግዥ መለያ ያቁጥር መ/ግ/01/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን እና ለሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ለ2017 በጀት አመት የሚውሉ የአላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች ጥቅል ግዥ ማለትም፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የፕሪንተር፣ የፎቶ ኮፒ ቀለሞች /ቶነሮች/ ሎት 3. የመኪና ዲኮር /ጌጣጌጥ/ እና የታፒሴሪ ዕቃዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እና መዋቢያ ዕቃዎች፣ ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ሎት 6. የሕንፃ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሎት 7. የፈርኒቸር /የቤትና የቢሮ ዕቃዎች/ ሎት 8 ብስክሌት፣ የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪው፣ ሎት 9. የመኪና ጐማና ካላማዳሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) በከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት በፓስታ በማሸግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት እና በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here