ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃችን ማለትም፡- 1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ 2. የጽዳት እቃዎች፣ 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 4. የመኪና ጎማ፣ 5. ዘመናዊ ፈርኒቸር፣ 6. የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
የግዠው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
የጨረታ ሰነዱን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 ድረስ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ረዳት ገንዘብ ያዠ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለተራ ቁጥር 1. ብር 15‚000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ ፣ ለተራ ቁጥር 2. ብር 1000.00 /አንድ ሽህ ብር/፣ ለተራ ቁጥር 3. ብር 4000.00 /አራት ሺህ ብር/፣ ለተራ ቁጥር 4. ብር 12000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር፣/ ለተራ ቁጥር 5. ብር 5.500.00 /አምስት መቶ ብር/፣ ለተራ ቁጥር 6. 10.000.00 /አስር ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገን/ጽ/ግዠ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ተጫራቾች ያወጡትን ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ወረዳው ድረስ በራሱ ማጓጓዝ አለበት፤ለፍትህም ሆነ ለማንኛውም አገልግሎት ያወጡትን ወጭ በራሱ የሚችል ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀናት ውጭ የሚመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ አይቀበልም፡፡
መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዋች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
እቃዎቹ በባለሙያ ተረጋግጠው ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሰራ ቀን ይከፈታል፡፡
አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታየ ቀናቶች ውስጥ ውል መያዝ እና የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
አሸናፊው ድርጅት ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር ይቆረጣል፡፡
ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምገም ለማጽደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስ/ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ 058 664 04 64 /002 መደወል ይችላሉ፡፡

የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here