በማእከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በምግብ ዋስትና በተገኘ የገንዘብ በጀት የድርማ ወንዝን ተከትሎ ከገበባ ሳልጅ ቀበሌ እስከ ሰራባ ዳብሎ ቀበሌ፤ መገጭ ወንዝን ተከትሎ ከአረቢያ አባሊባኖስ እስከ ወይና ጣና ቀበሌ እና ሱዳን ገደል ወይም አባ ገነን ወንዝ ተከትሎ ከጓንጃ እስከ ጓንጃ የጎርፍ አደጋን የመከላከል ሥራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ ተጨራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ7/08/2016ዓ.ም እስከ 27/08/2016ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትአዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታው ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዠ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ21ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ 27/08/2016 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ27/08/2016 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በግዠ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡ በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን በተጠቀሰው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ለጨረታው መሟላት የሚገባቸው ሁኔታወች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለው።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች /ተወዳደሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ሥራውን ማለትም የጎርፍ መከላከል ሥራውን መጀመር አለበት።
- ማንኛውም ተወዳደሪ የጎርፍ መከላከል በቀረበው የመጫረቻ ሰነድ በትክክል በማየት መወዳደር ይኖርበታል። የማሽኑ ዓይነት ኤክስካቫተር ባለ ሰንሰለቱ፣ የማሽን ማጓጓዣዎችን እና የናፍጣ ወጭዎችን በራሳቸው ወይም በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚትፈልጉ ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረዳት ይቻላል።