ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

በምሥ/ጎጃም ዞን የይማና ዴንሳ ወረዳ /ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለይ/ዴ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 4. የዉሃ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መጫረት ትችላላችሁ፡፡
የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢመሆን አለባቸው፡፡
በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ደ/የስራሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 338 02 98 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ የጽህፈት መሳሪያ 11,000.00፣ የጽዳት ዕቃዎች 8,000.00 ፣ኤሌክትሮኒክስ 24,000.00 ፣ እና የዉሃ ዕቃዎች 3,550.00 በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 23/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ፤ የተሞላበትን ፎርም ቲን ፤ የንግድ ፈቃድና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታዉ የሚዘጋው ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተጠቀሰው ቀን 4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ከመክፈት አያግደውም፡፡
አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አስር በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለበት፡፡
ተጫራቾች አሸገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት ወይም በጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ይሆናል፡፡

የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here