በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 4 የቧንቧ ውኃ እቃ፣ ሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ፣ ሎት 8 ቋሚ እቃ፣ ሎት እና ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃ በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ እና የሚጠገኑ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናን ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሪው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ከ 23/03/2017 እስከ 07/-04/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 08/04/2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻላ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ መለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ መምርያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባለው ንብረት መጋዘን በዝርዝር ማስረከብ የሚችል፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 03 54 /058 331 01 75 ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሥርዝ ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅረቦት ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ ይችላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል