የአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2017 ዓ.ም የሚሆኑ ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 2. አንቲ ቫይረስ፣ ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5. ፈርኒቸር፣ ሎት 6. ቢል ቦርድ፣ ሎት 7. የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ ሎት 8. የተሸከርካሪ ጎማ፣ ሎት 9. የብስክሌት ጎማ፣ ሎት 10. የህንፃ መሳሪያዎች እና ሎት 11. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ መወዳደር ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙም ሆነ የሚጠገኑ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50.00 (አምሳ) በመክፈል ከህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 14 /2017 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ስለሚቆይ የጨረታ ሰነድ በሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም በ3፡00 ታሽጎ ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን የሚገባቸው ሲሆን ይህም በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 218 02 61 ወይም 058 321 13 08 በሥራ ቀንና ሠዓት መጠየቅ ይቻላል፡፡
- አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ባ/ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጎን ኢትዮ ቴሌኮም ፊት ለፊት ነው፡፡
የአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ
ባሕር ዳር