ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

ቁጥር ግጨ 03/2017

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ለኔትወርክ ዝርጋታ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን አቅርቦ ከነዝርጋታው እና የደህንነት ካሜራና አክሰሰሪ ከነመግጠሙ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅት ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የእቃው ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎችን በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኝው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
  4. በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለሎት/ምድብ 01 ለኔትወርክ ዝርጋታ የሚያገለግሉ ዕቃዎች አቅርቦት ከነዝርጋታው ላይ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት /ምድብ 02 የደህንነት ካሜራ ከነመግጠሙ ላይ ብር 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው በገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፤ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ፡- አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 /058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here