ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በመደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ቋሚ እቃ፣ ሎት 5 የተዘጋጅ ልብሶች፣ ሎት 6 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 7 ቆዳ ጫማ እና  ሎት 8 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ  መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢን ቦድ እስከ 60 /ስልሳ/ ቀን ያላነሰ የሆነ ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ /ሲፒኦ/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ሁሉም ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ በድምር አሸናፊ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንድሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. መ/ቤቱ በያንዳንዱ ግዥ ላይ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  10. የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት እቃውን የሚያስረክበው በለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 033 114 02 83 /09 14 07 94 81 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች በፖስታው ላይ ቀን ፤ ስም ፤ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር የሚወዳደሩበትን ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 20/ ሃያ ብር/ በመክፈል ለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here