ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
98

ደ/ታቦር ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 የበጀት ዓመት ለማሰራት ካቀዳቸው የመንገድ ሥራዎች ውስጥ 1ኛ. ቀበሌ 04 ከሰጠኝ ቤት እስከ ሞገስ በዛ ቤት ሁሉን መንገዶች አስተሳስሮ ከተፋሰስ ጋር 1.4 ኪ/ሜትር እና 2ኛ. ቀበሌ 07 ከደ/ታቦር ዩኒቨርስው አስፖልት እስከ አምሳሉ ድረስ ቤት ከተፋሰስ ጋር 1.41 ኪ/ሜትር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በGC አና RC መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  2. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. ያቀረቡት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆነዎን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች በአንድ ፖስታ በማሸግ የተጫራቹን ሙሉ አድራሻ ማህተምና የሚወዳደሩበትን ፕሮጀክት ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠ/ዋጋ 260,000.00 /ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ ድጋፍ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያው ቢያስ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 /ዘጠና/ ቀን የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
  10. ዮጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 11/12 ይገኛል፡፡
  11. የጨረታ ሳጥኑ መሰረተ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ይገኛል፡፡
  12. የግል ኮንትራክተር ያሸነፈበት ዋጋ ቢያንስ አስራ አምስት በመቶ የመንግስት የልማት ድርጅት ቢያንስ ሃያ በመቶ ለተደራጁ ኢንተርኘራይዞች በሰብ ኮንትራት መስጠት አለበት፡፡
  13. የክልሉን ግዥ መመሪያዎች እስከ ማሻሻያቸው ተግባራዊ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያላሟላ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 91 /00 58/ 058 441 02 03 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የደ/ታቦር ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here