ደ/ታቦር ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 የበጀት ዓመት ለማሰራት ካቀዳቸው የመብራት ዝርጋታና የጥገና ስራዎች ውስጥ 1ኛ. ከፖሌ ቴክኒክ ከሌጅ እስከ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ጽ/ቤት የትራፊክ መብራት እና የዋናው መንገድ መብራ ጥገና 2.6 ኪ.ሜ 2ኛ. የተቋረጠው የዋናው መንገድ መብራ ዝርጋታ ሥራ እና በተመረጡ ቦታዎች 3 ትልልቅ የሃይ ማስት /ባውዛ (ቀበሌ 09 ከአፄ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ጽ/ቤት አስከ ዛጎል ማደያ) 0.56 ኪ/ሜትር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ኤሌክትሮ መካኒካል ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ያቀረቡት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይቻላል፡፡
- ጨረታው የቴክኒካል ግምገማና የፋይናንሻል ግምገማ ነው፡፡
- ተጫራቾች አስፈላጊውን እቃና ሰራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሰሩበትን የቴክኒክና የፋይናንሻል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአንድ ሌላ ማዘር ፖስታ በማሸግ የተጫራቹን ሙሉ አድራሻ ማህተምና የሚወዳደርበትን ኘሮጀክት ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በመደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሰረት በመንግስት ገቢዎች ባለ ስልጣል የተረጋገጠ የሂሣብ ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የቴክኒካል ሀሣብ የያዘ ሰነድ በመጠየቁ /ባዶ ቦታዎች/ ተሞልቶ ተፈርሞ እና ማህተም ተደርጎ እና አሽጎ ያልመለሰ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠ/ዋጋ ለተራ ቁጥር 1ኛ ብር 260,000.00 /ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር 2ኛ ብር 130,000.00 /አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ ድጋፍ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ቢያስ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 /ዘጠና/ ቀን የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 11/12 ይገኛል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ መሰረተ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ይገኛል፡፡
- የግል ኮንትራክተር ያሸነፈበት ዋጋ ቢያንስ አስራ አምስት በመቶ የመንግስት የልማት ድርጅት ቢያንስ ሃያ በመቶ ለተደራጁ ኢንተርኘራይዞች በሳብ ኮንትራት መስጠት አለበት፡፡
- የክልሉን ግዥ መመሪያዎች እስከ ማሻሻያቸው ተግባራዊ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያላሟላ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 91 /00 58/ 058 441 02 03 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደ/ታቦር ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ