ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳዳር ዞን የእንጅባራ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት የገቢ፣ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል፡- ሎት አንድ የደንብ ልብስ፣ ሎት ሁለት፣ ኦዲት ሥራ አገልግሎት፣ ሎት ሦስት ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት አራት እስቴሽነሪና የጽዳት መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎችን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዩች መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፊኬት የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የእን/ከ/ው/አገ/ጽ/ቤት ገቢ፣ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ባዘጋጀው የጨረታ መመሪያ ዝርዝር መሰረት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ዋጋ00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ዋጋ ሁለት በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ጨረታው ከወጣበበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን ማለትም ከቀኑ 4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከቀኑ 4፡30 እንጅባራ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ንዑ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 ይከፈታል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም የሚገልጽ ማህተም ስምና አድራሻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ በትክክል በመጻፍ ቢሮ ቁጥር 17 ለዚሁ ሲባል ለተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 51 38 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  11. በዘርፍ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ከፍሎ ፈቃድ ያሳደሱና እቃው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ አሸናፊ የምንለየው ሎት አንድ እስከ ሎት አራት ብለን የጠቀስናቸው እቃዎች አሸናፊ የምንለየው በሎት ዋጋ ነው፡፡
  13. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች የልዩ ልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያድርጓቸውን ወቅታዊ የሆነ እና ለጽ/ቤቱ በአድራሻ የተጻፈ ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነቱ በተገለጸበት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  15. አሸናፊ ድርቶች አሸናፊነቱ ተገልጾ ውል ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን እቃ ጥራቱን የጠበቀ ውሃ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  17. ተጫራቾች በጨረታው አፈጻጸም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ መመሪያ አንቀጽ 35 ን.አ.1 መሰረት አቤቱታ ማቅረብ መብት አላቸው፡፡
  18. ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ ለቀጣይ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የተጫራቾችን የመመሪያ የጨረታ የዋጋ ዝርዝር የውል ቃሎችና ሌሎች የሰነድ ደረጃ ተዘጋጅተው የተሸጡትን በሙሉ ከፖስታ ጋር አብሮ ህጋዊ ማህተም አድርጉ በተሟላ ሁኔታ ማስገባ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ሰነዱን ተመላሽ ባያደርጉም ለተጠቀሱት የውል ቃሎችና የተጫራቾች መመሪያ ተገዥ እንደሆነ ተቆጥሮ በውድድሩ ይሳተፋል፡፡

የእንጅባራ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here