የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የእንሰሳት ህክምና መሳሪያዎች እና ሎት 5 የዶሮ እርባታ እና የንብ ማነብ ሥራ ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማላት ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑና የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም እቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም እላቂ የጽህፈት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የተለያዩ ቀለሞችን እና ሌሎች በባለሙያ የሚፈተሹ እቃዎችን በራሳቸው ወጪ በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በሃላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሞሉትን ዋጋ አስር በመቶ መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ በሚነበብ መልክ መፃፍና በየገጹ ማህተም ማድረግ እና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን እንዲሁም ቫት ዊዝሆልዲግ ሰባት ነጥብ አምስት ታሳቢ ተደርጎ መሞላት አለበት፡፡
- ውድድሩ በድምር ዋጋ /ሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዶችን ለያንዳንዳቸው ሎቶች00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክራቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ ወይም የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽን የሚከፈት ይሆናል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ በመሆን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ የሞሉትን ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 በመሥሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰብ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ ለሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ስለሆነም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የተሳሳተ ሥርዝ ድልዝ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ክጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስቀጣል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 79 04 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ከሎት አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልበጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች የተቀበሉትን ናሙናዎች በማየት ዋጋ ሊሞሉ ይገባል፡፡
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ