ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

በሰሜን ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ አስተዳደር  የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት ሎት1. የግብርና እቃዎች፣ ሎት 2.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 5. የመኪና መለዋወጫዎች፣ ሎት 6. ኬሚካል ፣ ሎት 7. የላብራቶሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ  ህጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ  ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ
  5. የተጨማሪ  እሴት  ታክስ  (ቫት)  ከፋይነት  የተመዘገቡ  መሆናቸውን  የሚያረጋግጥ  የምስክር  ወረቀት  ማቅረብ  የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችው ጋር አያይዘው በፖስታ በማሸግ በማዕከሉ  የጨረታ  ሳጥን  ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የዕቃውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር  100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲ.ፒ. ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
  11. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት  ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ

ቀናት ይቆያል። ጨረታው  በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00  ታሸጎ በዚሁ ቀን 4፡30

በማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል። በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ስም አድራሻ የሚመለከተው (ህጋዊወ ኪል ) የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጦ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ እንዲወዳደሩ የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ካላቸው ከአንድ በላይ ሎት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ከተገለፀ ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም ያለባቸው ሲሆን ፣ ተጫራቹ አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ማዕከሉ ድረስ የመቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ አሸናፊውን ለመለየት ያመች ዘንድ በአንድ ሎት   ለቀረቡ እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ለበለጠ መረጃ 058 338 11 66 መደወል ይችላሉ::

የአዴት ግብርና ምርምር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here