በምሥራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ የድጎ ጽዮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 ዓ/ም በጀት አመት የባብጫ ጥልቅ ጉድዳድ የውሃ ጉድጓድ ዝርጋታ የHDPE እና መገጣጠሚያ እቃችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ 30/03/2017 እስከ 14/4/2017 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ማስገባት አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ ክፍል ቀን 15/04/2017 ዓ.ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡ የማይገኙ ከሆነም ይከፈታል የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሎት በድምር ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የሚያሰራዉን ሥራ ሃያ በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የበጀት ምንጭ ከድጎማ፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት በመወዳደሪያ ሀሳብ የእቃውን አይነትና የአምራቹን ስም የተመረተበትን ሀገር ያካትታል፡፡
- ለእቃው አቅርቦት ግዥ ከ10,000.00 (አስር ሽህ ብር) ግዥ በላይ ከሆነ አቅራቢው ከሚከፍለው ክፍያ ሁለት በመቶ የቅደመ ግብር ተቀንሶ ይቀራል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በየሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በማስፈር የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚገኝበት ቦታ ድጎ ፅዮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ጨረታ ያወጣዉን ተቋም መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ ወይም አገልገግሎት ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን እቃ ብዛት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ መግለፅ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስር በመቶ የጠቅላላ ዋጋ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ያላስያዘ እና ያልፈፀመ እንደሆነ ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታ ማስከበሪያውን በመውረስ ለ2ኛ አሸናፊ የመስጠት መብት አለው፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች እቃዉን ድጎ ፅዮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድረስ አቅርቦ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች የእቃዉን ትራንስፖርት በራሱ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያዉን ከተገለፀዉ ቀን ቀድሞ በተዘጋጃዉ የጨረታ ሳጥን የሚመልስ ከሆነ ከተገለፀዉ አሸናፊ የመለየት ቀን ቀድሞ አሸናፊ ሊለይ ይችላል፡፡
- ዋናውን የጨረታ ሰነድ በፖስታ በማሸግና በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ማህተም እና ሙሉ አድራሻ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 254 00 56 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የድጎ ጽዮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ