ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
156

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ የላብራቶሪ የሥራ ክፍል ጣሪያው ስለፈራረሰ በአዲስ ለማሠራት በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅቱ ውል ይዞ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም፣ የድርጅቱ ማህተም እና አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመጻፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመሥሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 25 በመምጣት የጨረታ ሰነድ በመውሰድ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት በመስረያ ቤታችን በመምጣት ገቢ ማድርግ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም የጨረታ ሰነድ የወሰዱ ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው መመለሳቸው ከተረጋገጠ ሙሉ የጨረታ አየር ሰዓት መጠበቅ ሳያስፈልግ ይሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመሥሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን 07/08/2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም 22/08/2016 ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. የሚሠራው ጣሪያ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  11. አሸናፊው ጣሪያ ሥራውን በተገቢው መንገድ ሰርቶ ሲጨርስና ትክክለኛነቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ክፍያው የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾቹ ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበባቸው መሆን አለበት፡፡
  13. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፤ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  14. ከመሃንዲስ ዋጋ ግምቱ በላይ የተጋነነ ዋጋ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 23 22 10 87/ 09 18 21 06 28/ 09 18 22 05 04 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here