የደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ማለትም በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የፋይል መደርደሪያ እና ህትመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መ/ቤቱ ባወጣው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ኮፒውን እና የዋጋ መሙያቸውን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት ከዋና ገ/ያዥ ብር 00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 05 79 24 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ጠቅላላ ዋጋ 0.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ በሁኔታው ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሣቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል ጨረታው የሚከፈትበት በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡዋቸውን የመጫረቻ ዋጋዎች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ያልተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቹ የሞላውን ዋጋ ሳይለውጥ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች ደ/ማ/ከ/አስ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ግዥው በሎት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደብረ ማርቆስ ወረዳ ፍ/ቤት