ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
124

የደ/ታቦር ደም ባንክ አገልግሎት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም የመኪና ጎማ፣ ህትመት፣ የታሸገ ውሃ፣ የፆም ክሬም ያለው ብስኩት፣ የጽዳት እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የደም ማስለገሻ አልጋ እና ሌሎች ተመሳሳይ አቅርቦቶችን በዘርፍ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የተሟላ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ጠቅላላ የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያም በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  2. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለግባቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በጀርባው ላይ ከኦሪጅናሉ ጋር ተገናዝቧል ብለው በመፃፍ ስማቸውን፣ ቀን እና የድርጅቱን ማህተም አድርጎ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20.00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ደ/ታቦር ደም ባንክ ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያው ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የእቃው ዓይነት ሰነዱን ሲገዙ የምናሳውቅ ሲሆን ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  7. ተጫራቾች ለውድድር ከቀረቡ በኋላ ሃሳባቸውን መለወጥ /ማሻሻል ወይም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ፖስታው ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ ደ/ታቦር ደም ባንክ ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስታወቂያው ከወጣበት 7/4/2017 ዓ/ም የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም እስከ 22/4/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ወይም በድምር ዋጋ ነው፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የእቃውን ዝርዝር ዋጋ ሁሉንም ሎት መሙላት አለባቸው፡፡ ሁሉንም ያልሞላ ግን ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ ከደም ባንኩ ድረስ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አሸናፊነታቸው ከተነገራቸው በኋላ በ5 /አምስት ቀን/ ውስጥ እቃውን ለማቅረብ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ካላደረጉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ታቦር ደም ባንክ ግ/ኦፊሰር ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 141 02 71 /09 33 22 04 86 /09 24 27 28 26 በመደወል መረጃ ማግኘት  ይችላሉ፡፡ አድራሻችን ኡራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

የደብረታ ታቦር ደም ባንክ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here