የአብክመ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ለቢሮዉ የሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 የተሸከርካሪ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት 01 እና 04 ለተዘረዘሩት 30,000.00 /ሰላሳ ሽህ ብር/ እና ሎት 02 እና 03 ለተዘረዘሩት 15,000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ግምገማ ዘዴው ሎት 01 በነጠላ ዋጋ ሲሆን ሎት 2፣3 እና 4 በጠቅላላ ዋጋ /ሎት/ እንደሚሆን ታሳቢ በማድረግ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 37 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሰነድ የወሰዱ ተወዳዳሪዎች የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ፤ፌርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ሎት 01 ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸው በሁለት ፖስታ ማለትም ፋይናንሻል እና ቲክኒካል ለየበቻ በማሸግ ቲክኒካልና ፋይናንሻል በማለት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከ07/04/2017 ዓ.ም እስከ 21/04/2017 ዓ.ም በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ22/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ45 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 08 17 /058 320 74 34 በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ቀበሌ 8 ባ/ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 37 ነው፡፡
የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ
ባ/ዳር