በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ዉስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ፣ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ፣ሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ፣ ሎት 5 የማሽን ኪራይ እና የመንገድ ጥገና ሥራ በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ለማሰራት /ለመግዛት/ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- የተሰጣቸው የንግድ ሥራ ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የቲን ናምበር፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቫት/ ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ሁሉም የእቃ አቅርቦትና የግንባታ ዕቃዎች ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የእቃ አቅርቦት ሥራዉን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መስራት /ማቅረብ/ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸዉን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገዉና ማህተም አድርገዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚፈለገዉ ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታዉ ላይ ዋናዉንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተዉ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ለዕቃ ግዥ በሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ለግንባታ ሥራዎች በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ ገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡ ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 18,000.00 /አስራ ስምንት ሽህ ብር/፣ ለሎት 3 ብር 1500.00 /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር /፣ ለሎት4 ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሽህ ብር/ እና ለሎት 5 ብር 45,000.00 /አርባ አምስት ሽህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታዉ ጋር ለብቻዉ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ሥራ የጽሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ላሉት የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 06 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለዕቃ ግዥ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ለመንገድ ጥገና ሥራዎችና ለማሽን ኪራይ ሥራዎች ለ30 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ31ኛው ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን /ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አቅርቦቱን ለማቅረብ /ለመስራት/ ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ በገቡት ውል መሰረት ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከአሸነፉበት ዋጋ የዋጋ ልዩነት ቢኖር ምንም አይነት ጭማሪ የማናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊዉ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለዉል ማስከበሪያ የሚሆን ለዕቃ ግዥ አስር በመቶ እና ለመንገድ ጥገና ሥራዎችና ለማሽን ኪራይ /ለግንባታ ሥራዎች/ ሃያ አምስት በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለእቃ አቅርቦት /ለአገልግሎት/ ለግንባታ ሥራዎች 40 /አርባ ቀናት/ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 247 01 13 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት