በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣ሎት 2 አላቂ የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 የኤልትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት 4 የመኪና ጎማ ፣ሎት 5 የኤክልትሮኒክ እቃዎች ጥገና እና ሎት 6 የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ የመወዳደሪያ መስፈርቶችም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ (አንድ ወጥ በሆኑ) ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 22/04/2017 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን 22/04/2017 ዓ/ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ስለ ጨረታ የተሻለ ዘዴ /አማራጭ / ከአገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 23 50 60 /09 48 47 78 83 /09 23 77 63 77 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ማብራሪያ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት