ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
115

ቁጥር ግ/ጨ/መ/ቁ/01/2ዐ17

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ   የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የህትመት ሥራ   ግዥዎችን በፕሮጀክት ፣ በመደበኛ ካፒታል እና በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ በእያንዳንዱ የግዥ አይነት ዘርፍ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታውን ሠነድ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ  ቀናት                                                                                                        ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀበሌ 8 ጋምቢ ቲቺንግ ሆስፒታል አጠገብ ከሚገኘው መሬት ቢሮ  ቢሮ ቁጥር  18 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ቅጽ መሰረት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው  መሠረት  ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ  ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት የመጨረሻ ቀን 3፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚያገለግል ለጽህፈት መሳሪያ 300,000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 500,000.00 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ለጽዳት እቃዎች 15,000.00 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ለህትመት ሥራ ግዥ 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ለመኪና ጎማ 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ደረሰኙን ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡፡
  6. ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የግዥ መጠናቸው ጠቅላላ ከ20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ለሚሆን ግዥ ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ (ቫቱን) ተቀናሽ እናደርጋለን፡፡
  9. በጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሰረት በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በየ በጀት አርስቱ የተዘጋጀውን የዋጋ መሙያ ቅጽ ከሞሉ በኋላ ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በአንድ ፖስታ ጨምሮ ማቅረብ ሳይሆን ለእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ቅጽ ሰነዶችን ጨምሮ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 71 31 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  መሬት ቢሮ

ባ/ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here