ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
123

በደቡብ ወሎ ዞን በመቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ በ2017 በጀት አመት የሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ የገረጋንቲ መንገድ ሥራ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማሽኖች አስከ ዝርዝር መገለጫቸውን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የማሽኖቹ አይነት የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1ኛ. ምፕትራክ/ ገልባጭ  መኪና ሲኖ ትራክ /ጎማቸው አድስ የሆነ  በጠቅላላ  16 ሜትር ክዩብ  መያዝ  ያለበት ሲሆን  ከሚሰራበት  ሳይት  በአማካይ 6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ማቴሪያል የመጫን ሥራ ማቅረብ ያለበት ሲኖ ከ/8/ ስምንት በላይ መሆን አለበት፡፡ በጠቅላላው 1777.5 ቢያጆ፣ 2ኛ. ሞተር ግሬደር /cut ሰዓት 300 (ሶስት መቶ) ሰዓት፣ 3ኛ. ቫይብሬተር ሮለር / 14 ቶን በላይ ክብደት ያለው በሰዓት /250/ (ሁለት መቶ ሀምሳ) ሰዓት፣ 4ኛ. ዊል ሎደር 3 ሜትር ኪውብ መያዝ የሚችል ሰዓት 250 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሰዓት)፣ 5ኛ. የውሀ ቦቲ /18000 ሊትር የሚይዘ (አስራ ስምት ሺህ ሊትር) 50 ቢያጆ መሆን አለበት እና 6ኛ. ኢክስከቫተር ከነ ጃክሀመሩ /እግሩ የሰንሰለት የሆነ 305 (ሶስት መቶ አምስት) እና በላይ መሆን አለበት፡፡ የሥራው ሰዓት /400 (አራት መቶ) ሰዓት ነው፣ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ማሽኖች 2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረቱ ምርት ማቅረብ የሚችሉና የቴክኒክ ችግር የሌለባቸው መሆኑን በማረጋገጥ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተፈላጊ ችሎት

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው 2016 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው 2016 ዓ.ም የሥራ ግብር ክፍያ የከፈሉ፡፡
  2. የጨረታ መጠን ወይም የግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ክፍያ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃውን ጠቅላለ  ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና  ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ወይም ሃያ አምስት በመቶ ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. በማሸጊያ ፖስታ ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስፈር ያስፈልጋል፡፡

ሀ. የጨረታውን አይነትና ቁጥር፣

ለ. ጨረታውን ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ፣

ሐ. የተጫራቾችን ስም ፊርማና ሙሉ አድራሻ፣

መ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ በማሸግ  ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤቱ ህጋዊ ሰነድ ገቢ ተደርጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

  1. በፖስታው የሚላክ የመጫረቻ ሰነድ በመዘግየቱና በጥንቃቄ ካለመታሸጉ ጋር በተያያዙ ችግሮች መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ /ተመስርቶ/ መጫረት አይችሉም፡፡
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች አስፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና የሚያቀርቡበትን የመጫረቻ ሰነድ በጨረታ ሰነዱ የተመለከተውን የዕቃ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመጠቀም በተገለፀው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ተለይቶ በዝርዝር በመሙላት በመፈረምና በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለም ስለመስተካከሉ ፖራፍ መደረግ አለበት፡፡
  5. እያንዳንድ ዋጋ የሚሞላው በነጻ ገበያ ላይ ተመስረቶ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የማሽን የቴክኒክ ብልሽት ፤ የስፔር ፓርቶች ለውጥ እንዲሁም ዘይት ነክ ነገሮች እና የነዳጅ ወጭ ተጫራቹ በራሱ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የአንድ ማሽን ሙሉ የሥራ ወጭ ዋጋ እና የጠቅላላ ማሽን የሥራ ወጭ ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ተጫራቹ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
  8. የማሽን ኪራይ ሰዓት የሚቆጥረው ለሥራው ሥራ ሰዓት ብቻ ነው (የተፈጥሮ አደጋዎች ዝናብ እና ተያያዥ ችግሮች ከተከሰቱ የሚባክነው ሰዓት አይያዝም ወይም የማይቆጠር ይሆናል፡፡
  9. የማጓጓዣ፣ የመጫኛ እና ማውረጃ ሎቤድ እና ከሚሰራበት ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ሳይት ሌሎች ወጭዎችን ተጫራቹ የሚችል ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የሹፌር እና የኦፕሬተር እንድሁም የረዳት አበል እና ሌሎች ወጭዎችን ተጫራቾች የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  11. እያንዳንዱ ማሽን የሚቀርበው በሥራው ቅደም ተከተል መሰረት ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ጨረታ ለማሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድርግ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅርብ አለባቸው፡፡
  13. የዕቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁት በአማረኛ ቋንቋ ነው፡፡
  15. የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቦታ ደ/ወሎ ዞን መቅዳላ ወረዳ ማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት 07/04/2017 ዓ.ም እስከ 27/04/2017 ዓ.ም 11፡00 ድረስ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ መረጃዎችን በጥንቃቄ በመሙላት እና አድራሻ በመጻፍ በፖሰታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለበቸው፡፡ በ22ኛዉ ቀን 3፡30 ይዘጋል፡፡ በዚህ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በቀን 28/04/2017 ዓ.ም በይፋ ይከፈታል ነገር ግን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  16. ጨረታን ለማደናቀፍና የጨረታ ጊዜን ለማጓተት የሚሞክር ተጫራች በግዥ መመሪያው መሰረት ህጋዊ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 08 88 00 92 /09 14 54 38 72 /09 42 81 62 11 /09 46 29 22 53 ማገኘት ይችላሉ፡፡

የማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here