የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት አመት 1ኛ. የዳኞች ካባ 2ኛ. ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 11 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከታህሳስ 07/2017 እስከ ታህሳስ 21/2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 50 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 08 64 99 67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት