ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
116

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ስር ለሚገኙ 12 ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ለ3,895 የቅድመ አንደኛና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በቀን አንድ ጊዜ 200 ሚሊ ሊትር ፓስቸራይዝድ ወተት እና 100 /አንድ መቶ ግራም/ የፍርኖ ዱቄት ዳቦ   በግልጽ ጨረታ በማወዳደር እንዲቀርብ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ/ቲን/ ያላቸው ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ትምህርት ቤቱ ድረስ በቀን አንድ ግዜ ትምህርት ቤቱ በሚያመቻቸዉ ስዓት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 39 በመክፈል ሰነዱን 46 ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00/ሀምሳ ሺ ብር / ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናል ሰነድ በግልፅ ጽሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 46 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ቢ ቁጥር 46 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  8. ስርዝ ድልዝ የበዛበት እና አጠራጣሪ ቁጥር ያለው የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስል/ቁ/ 058-220-93-73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የባ/ዳር ከተ/ አስ/ ገን/ መምሪያ

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here