የግዥ መለያ ቁጥር አብክመ /ሳቴኮ/ግ/ጨ/ 02 /2017
በአብክመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ለተለያዬ አገልግሎት የሚውሉ ሶፍትዌሮችን ማለትም ሎት 1. የኢንቨስትመንት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር፣ ሎት 2. የፕሮጀክት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማስለማት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚወዳደሩበት የሶፍትዌር ልማት ግዥ ጥቅል ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚለሙ ሶፍትዌሮችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግፕት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢ/ቁ/02 በመምጣትና የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የሲስተም ልማት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን ፣የንግድ ፈቃድ ሰነድ ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሌላ ፖስታ ለየብቻ በታሽጉ ሁለት ፖስታዎች በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው ለሎት 1 እና ለሎት 2 ለየብቻ (በነጠላ ዋጋ) አሸናፊ የሚለይ ይሆናል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በቴክኒካል ሰነዳቸውም ሆነ በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 68 56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን