ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
122

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት ግዥ የሚውሉ ማለትም ፡-የጉልበት /የቀን ሰራተኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉን ፣ኮፒውን እና ሲፒኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ. ፎቅ ቢሮ ቁጥር 200–02 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ድረስ በተጠየቀው ልክ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 205079 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 08 ከዊዝደም ወደ ፖሊ መሄጃ አማራ ባንክ የተከራየበት ህንጻ ነው::

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት /ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here